ጥቃት እየደረሰብኝ ነዉ?
የቤት ዉስጥ ጥቃት እየደረሰቦት ከሆነ፣ የእርሶ ጥፋት አይደለም፡፡ ጥቃት ሊደርስቦት አይገባዎትም፡፡ ድጋፍ አለ፡፡
የቤት ዉስጥ ጥቃት ተከታታይ የማስገደድ ባህሪ ሲሆን አንድ ሰዉ ሌላ ሰዉ ላይ፣ አብዛኛዉ ጊዜ የፍቅር ጓደኛ ላይ አካላዊ፣ስነ አእምሮዊ፣ ስሜታዊ፣ ቃላዊ፣ ፆታዊና ኢኮኖሚያዊ የበላይነትና መቆጣጠር ባህሪ ይገለፃል፡፡
የቤት ዉስጥ ጥቃት ምንድን ነዉ?አካላዊ ጥቃት::
መምታት, ጥፊ መምታት , መራገጥ, ማነቅ, መግፋ, በቦክስ መምታት, መደብደብ.
ቃላዊ ጥቃት::
የማያቋርጥ ነቀፌታ, ማሾፍ, የሚያዋርድ አስተያየት ማድረግ, መጮህ, መራገም, ስም- ምስጠት, ማቋረጥ,
ፆታዊ ጥቃት::
ግብረስጋ ግንኙነት ማስገደደ, ፆታዊ እንቅስቃሴ ማስገደደ, ክብር እሚነካ አያያዝ
መነጠል::
ጓደኞችና ዘመዶች እንድያገኞቸዉ ማክበድ, የስልክ ጥሪ መከታተል, መልእክት፣ ፅሑፍ፣ ወይ የፅሁፍ መልእክት ማንበብ, የቀንበቀን እንቅስቃሴ መቆጣጠር, ቁልፍ መቆጣጠር, ፓስፖርት ወይ ዶክሜንቶችን ማጥፋት
ማስገደደ::
ጥፋተኝነት ስሜት መፍጠር, ትካዜ, ህጻናትንና የቤተሰብ አባላተትን እንደፈለጉ ማድረግ, ሁሌም እዉነት ነኝ ማለት, እማይፈፀሙ ‹ህጎች› መፍጠር
መድባት/እገዳ::
ማየት ወይ መከታተል, የማስፈራርያ ጥሪዎች ወይ እማይፈለጉ የፅሁፍ መልእክቶች መደጋገም, ማሕበራዊ ግንኙነቶን መከታተል, በድህረ ገፅ ላይ የእርሶን አላስፈላጊ ፎቶ ወይ ቪድዮ መለጠፍ, እማይፈለጉ ስጦታዎችን መላክ, ቤቶን ሰብሮ መግባት ወይ ንብረቶን ማጥፋት, በቤቶ ዉስጥ ካሜራ ወይ ስልክና ኮምፒተሮ ላይ የስለላ እቃዎች መጠቀም
ኢኮኖሚያዊ ቁጥጥር::
ክፍያዎችን አለመክፈል, ብር ለመስጠጥ እምቢተኝነት, አለመፍቀድ፡, ወደ ትምህርት ቤት መሄድ, ወደ ስራ መሄድ, የስራ ክህሎት መማር, ለመስራትና ቤተሰብን ለመርዳት እምቢተኝነት
እምነትን ያላግባብ መጠቀም::
መዋሸት, ቃልን መስበር, አስፈላጊ መረጃ መደበቅ, ታማኝ አለመሆን, ቅናተኛ መሆን, የቤት ዉስጥ ሓላፊነት አለመጋራት
ዛቻና ማስፈራራት::
ሌሎችን ለመጉዳት ዛቻ, የቤት እንስሳትን ለመጉዳት ዛቻ, ለማስፈራራት አካለዊ መጠን መጠቀም, መጮህ, የጦር መሳርያ ማስቀመጥና እንደሚጠቀሙበት ማስፋራራት
ስሜትን ከመግለፅ መገታት ::
ስሜትን አለመግለፅ, አስተያየት አለመስጠት, ትኩረት አለመስጠት, ስሜቶች፣ መብቶች፣ ሓሳቦችና ምልከታዎችን አለማክበር
ንብረት ማዉደም::
የቤት እቃ ማዉደም, ግድግዳ መምታት, ነገሮችን መጣል ወይ መስበር, እንስሳትን ማጥቃት
ራስን ማጥፋት ባህሪ::
ሓሺሽ ወይ አልኮል መጠቀም, ራስን ለመጉዳት ወይ ራስን ማጥፋት ማስፈራራት, ያለጥንቃቄ ማሽከርከር, ችግር መፍጠር
ተጠቂዎቹ እነ ማን ናቸዉ?
ማንኛዉም ሰዉ ተጠቂ ሊሆን ይችላል ጥናቶች እንደሚያሳዩት የቤት ዉስጥ ጥቃት እሚደርስባቸዉና የግል ባህሪ ዓይነት ጋር ግንኙነት አልተገኘም፡፡ የቤት ዉስጥ ጥቃት እሚደርስበትን ሰዉ ባህሪ በመቀየር ጥቃት ሊቆም አይችልም፡፡ ሁሉም ሰዉ ከቤት ዉስጥ ጥቃት ደህንነቱ መጠበቅ አለበት፡፡
ሴቶች
- • ሴቶች በአጋራቸዉ የመጎዳት ወይ የመገደል ከፍተኛ አደጋ ዉስጥ ናቸዉ፡፡
- • ሴቶች በአጋራቸዉ የመጎዳት ወይ የመገደል ከፍተኛ አደጋ ዉስጥ ናቸዉ፡፡
- • በተለይ ነፍሰጡሮችና አራስ ሴቶች አደጋ ላይ ናቸዉ፡፡• ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በታች የሆኑና ወጣት ሴቶች የዴተንግ አደጋ ላይ ናቸዉ፡፡
ህፃናት
- እነሱ ራሳቸዉ ጥቃት ሊደርስባቸዉ ይችላል፡፡
- እነሱ ራሳቸዉ ጥቃት ሊደርስባቸዉ ይችላል፡፡
- ወላጆቻቸዉ ጥቃት ሲደርስባቸዉ ሊያዩ ይችላሉ፡፡
- ጥቃት አድራሹ ህፃናቱን እንደሚጎዳቸዉ ሊያስፈራራቸዉ ይችላል፡፡
- ትላልቆቹ ጥቃትን እንደተለመደ አድርጎ ማየት፡፡
ከ13 እስከ 19 ዓመት የሚገኙና ትንሽ አዋቂ
- ከ13 እስከ 19 ዓመት ያሉ ልጆች ለግንኙነት ጥቃት ተጋላጭና አደጋ ላይ ናቸዉ፡፡
- ከ13 እስከ 19 ዓመት ልጆች አዋቂዎችን ስለማያምኑ ድጋፍ ላይጠይቁ ይችላሉ፡፡
በ LGBTQ ግንኙነት ላይ ያሉ ሰዎች
- በ LGBTQ ግንኙነት ዉስጥ ያሉ ሰዎች በስትሬት ሴቶች በሚደርሰዉ የቤት ዉስጥ ጥቃት መጠን ያህል ይደርስባቸዋል፡፡
- በ LGBTQ ግንኙነት ዉስጥ ላይ ያሉት እርዳታ ላይጠይቁ ይችላሉ ምክንያቱ እርዳታ እንዳለ ስለማያምኑ ወይ መገለልን ስለሚፈሩ ነዉ፡፡
ትላልቅ አዋቂና አካል ጉዳት ያላቸዉ ሰዎች
- በአጋራቸዉ ወይ በባለቤቶቻቸዉ፣ አዋቂ ህፃናት፣ ወይ ተንከባካቢዎች ጥቃት ሊደርስባቸዉ ይችላል፡፡
- ራሳቸዉን ለመከላከል ወይ ከጥቃቱ ለማምለጥ አካላዊ ብቃት ላይኖራቸዉ ይችላል፡፡
- ጥቃቱን ለማንም ለመዘገብ አካላቸዉ ወይ አእምሮዋቸዉ ላይችል ይችላል፡፡
- አካል ጉዳት ያላቸዉ ወንዶችና ሴቶች ጥቃት ሊደርስባቸዉ እሚችልበት ትልቅ አደጋ ላይ ናቸዉ፡፡
ጥቃት ፈፃሚዎቹ እነማን ናቸዉ?
ጥቃት ፈፃሚዉ ‹ከቁጥጥር ዉጪ› አደሉም
- ጥቃት ፈጻሚዉ ለሁኔታዉ እንዴት መመለስ እንዳለበት ይመርጣል፡፡ በሃይለኛ ሁኔታ ለመፈፀም ሊወስኑ ይችላሉ፡፡
- ጥቃት ፈጻሚዉ ለሁኔታዉ እንዴት መመለስ እንዳለበት ይመርጣል፡፡ በሃይለኛ ሁኔታ ለመፈፀም ሊወስኑ ይችላሉ፡፡
- ተግባራቸዉ ከንዴት የመነጨ ብቻ አይደለም፡፡• ለጭንቀት መልስ እየሰጡ ብቻ አይደለም፡፡
- ያለድጋፍ በሃሺሽና አልኮል ተፅኖ ስር ስለሆኑ አይደለም፡፡
ጥቃት እሚማሩት
- ‹በተፈጥሮ› አይደለም፡፡
- ‹የተለመደ› አይደለም፡፡
- አንዳንድ ጊዜ ጥቃት ፈፃሚዉ ካደገበት ቤት ሊማር ይችላል፡፡
ጥቃት ፈፃሚዎች ሁኔታ፡
- ይቅርታ ሊሉና ፍቅር እሚሰጡ ሊያስመስሉ ይችላሉ፡፡
- ጠንካራ ሰራተኛና ጥሩ አቅራቢ መሆን፡፡
- ቀልደኛ፣አማላይ፣ ማራኪና ብልህ መሆን፡፡
- አንድ ወቅት፣ ፍቅር እሚሰጥ ወላጅ መሆን፡፡
የቤት ዉስጥ ጥቃት ተፅኖ
አብዛኛዉ ጊዜ የቤት ዉስጥ ጥቃት አእምሮ እሚያዛባ ነዉ፡፡ ‹አእምሮ መዛባት› እሚለዉ ቃል ያንድን ሰዉ የሆነ ሁኔታ ወይ የሁልግዜ ሂወት የመቻል አቅም የሚያሳዝን ወይ እሚበጠብጥ ሁኔታ ነዉ፡፡
ከቤት ዉስጥ ጥቃት ጨምሮ ከአእምሮ መዛባት የዳኑ፣ ‹የመዳን ሁኔታ› ዉስጥ ሊሄዱ ይችላሉ፣ ይህ ሶስት አማራጮች ይፈጥራል፡
- ታገል፡ አጋሮ እርስዎ ላይ ስላደረሰቦት ነገር ንዴት ሊሰማዎት ይችላል፡፡
- ሽሽት፡ ስለተፈጠረዉ ነገርና ሊፈጠር በሚችለዉ ነገር ሽብር ወይ ፍርሃት ሊሰማዎት ይችላል፡፡
- ተረጋጋ፡ የመደንዘዝ ስሜት፣ ራስን መግለፅ አለመቻል፣ ወይ መድረቅ ሊሰማዎት ይችላል፡፡
እነዚ የአእምሮ መዛባት አፀፋዊ መልሶች የተለመዱ፣ ተመሳሳይና በቀላሉ የሚረዱት ነዉ፡፡ አንድ መጥፎና እሚያስፈራ ነገር እርሶ ላይ ተፈጥሮል፡፡ ያስታዉሱ፡ ይህንን እንዲፈጠር አላደረጉም፡፡
ድጋፍ ከፈለጉ ምን መጠበቅ አለቦት
ጥቃት ያለበት ግንኙነት ላይ ከሆኑ ምን ማድረግ እንዳለቦት መወሰን ቢከብዶት የተለመደ ነዉ፡፡ ብቻዎትን አይደሉም፡፡ ድጋፍ ቀርቦለታል፡፡
በሜሪላንድ የሚገኘዉን የቤት ዉስጥ ጥቃት ፕሮግራም ጋር ሲደዉሉ ምን ይጠብቃሉ
ሃገር አቀፍ የቤት ዉስጥ ጥቃት ድጋፍ መስመር ወይ አካባብያዊ የቤት ዉስጥ ጥቃት ኤጀንሲ ጋር ሲደዉሉ እሚያስብ ሰዉና በሁኔታዎ ሳይገመግሞ በጥንቃቄ የሚሰማዎትን ሰዉ ያወራሉ፡፡ ደጋፊዎቹ ስላሎት አማራጮችና እሚወሰዱ ሂደቶችና ለርሶ ከሚጠቅም አገልግሎቶች ለመለየት ይረዳዎታል፡፡
ደጋፊዎቹ ስለ ሁኔታዎ ለማወቅ ጥያቄ ሊጠይቁ ይችላሉ ነገር ግን የእርሶን መሪነት ይከተላል፡፡ ለእርስዎ ጥሩ የሆነዉን እንደሚያቁ ባያስቡም፣ ለእርሶና ልጆቾ ጥሩ ሂደትና የተግባር ዉሳኔ እንዲወስኑ፣ ሁሉኑም ሊሆኑ የሚችሉ የወደፊት ሁኔታዎችና ዉጤቶች ግምት ዉስጥ እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ፡፡
እያንዳንዱ ሰፊ የቤት ዉስጥ ጥቃት ኤጀንሲ ከሁሉም ዘር፣ ብሄር፣ ዕድሜ፣ ፆታ፣ ማንነት፣ የፆታ ፍላጎት፣ ችሎታ፣ ባህል፣ መነሻ፣ ባህልና ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ መነሻ ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ አገልግሎቱ ነፃና ሚስጢር ናቸዉ፡፡ ዶክሜንት ከሌሎት ወደ ኢሚግሬሽን ፣ICE ፣ ወይ የሕግ አስከባሪ ሪፖርት አይደረግቦትም፡፡
ሰፊዉ የቤት ዉስጥ ጥቃት ኤጀንሲ ከሚከተሉት ጥቂት አገልግሎቶች ሁሉኑም ያቀርባል
ፈጣን መስመር
አብዛኞቹ አካባብያዊ ፕሮግራሞች ለችግሩ ድጋፍ፣ ማበረታት፣ መረጃና ለሪፈራል 24/7 ፈጣን መስመር አላቸዉ፡፡ ወደ ፈጣን መስመር ለመደወል ችግር ዉስጥ መሆን የለቦትም፡፡ በተጨማሪም ለዳኑና ድጋፍና መረጃ የሚያስፈልጋቸዉ ጓደኛ ወይ የቤተሰብ አባላት ወደ ፈጣን መስመር መደወል ይችላሉ፡፡
ደህንነት ማቀድ
የደህንነት እቅድ ግላዊና የመጎዳት አደጋ ለመቀነስ ተግባራዊ እቅድ ነዉ፡፡ በቤት ዉስጥ፣ ትምህርት ቤት፣ መስርያ ቤትና ማሕበረሰቡ ዉስጥ ራሶንና ልጆቾን በይበልጥ ለመጠበቅ ነገሮችን ለመለየት ያግዞታል፡፡ የደህንነቶ እቅድ በማንኛዉም ሰዓት ሊቀየር ይችላል፣ በግላዊ ሁኔታዎ መሰረት የሚቀያየር ሂደት ነዉ፡፡
ድጋፍ ቡድን
አብዛኞቹ ፕሮግራሞች የድጋፍ ቡድኑ የዳኑትን እንዲቋቋሙ፣ ልምዳቸዉን እንዲያካፍሉና ለደህንነት አማራጭ እንዲፈልጉ ያፋጥናሉ፡፡
መጠለያና የቤት አማራጮች
ደህንነቶ አደጋ ዉስጥ በመሆኑ ምክንያት ከቤት ዉስጥ መዉጣት ካለቦታት ደህንነቱ የተጠበቀና ሚስጥራዊ ቤት ይገኛል፡፡ እዛ በሚሆኑበት ግዜ ደህንነት እቅድ፣ ምክር፣ ቡድን ድጋፍና ለቀጣይ ደህንነቱ የተጠበቀ ምርጫ መፈለግ ላይ እሚያግዞትን ያገኛሉ፡፡
ፍርድ ቤት ድጋፍ
የፍርድ ቤት ድጋፍ በወንጀል ፍርድ ቤት ሂደት እሚጠበቀዉን ይገልፃል እንዲሁም የፍርድ ቤት ስርዓት ይመራዎታል፡፡ መረጃ ያለዉ ዉሳኔ ለመወሰን እንዲያግዞት፣ ስለ ሰቪል እገዳ ትእዛዝ እንዲሁም የወንጀል ጥበቃ ትእዛዝ ጨምሮ ስለ ፍርድ ቤት ጉዳይ መረጃ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ አንድአንድ የሜሪላንድ ፕሮግራሞች ከፍቺ፣ የይገባኛል ክርክርና ሲቪል ጉዳዮች የወጡ ሰዎችን ለማገዝ በተጨማሪ የቤት ዉስጥ ጠበቃ አላቸዉ፡፡
ምክርና የድጋፍ ቡድን
አብዛኞቹ ፕሮግራሞች አስተሳሰቦንና ስሜቶን እንዲፈትሹበት የሚደግፍ አካባቢ በማቅረብ እና እንዲሁም ለእርሶና ለቤተሰቦ ሃብትና ድጋፍ የሚያቀርቡ የቤት ዉስጥ፣ የግል ምክር ያቀርባሉ፡፡ በተጨማሪም አብዛኞቹ የቡድን ድጋፍ ይሰጣሉ፡፡
ፖሊስ ጋር ሲደዉሉ ምን ይጠብቃሉ
ሁሌም የህግ አስከባሪዎች ዓላማ የተጎጂዎችን ደህንነት መጠበቅ ነዉ፡፡ አብዛኞቹ የፖሊስ ክፍሎች ስለ ቤት ዉስጥ ጥቃት የሚደረጉትን ጥሪዎች በፍጥነት የመመለስ ጥቅም ይገነዘባሉ፡፡ በቦታዉ ሲደርሱ መጀመርያ የሚያደርጉት ነገር ተጨማሪ ጉዳት እንደማይፈጠር ማረጋገጥ ነዉ፡፡
በመቀጠል ምን ማድረግ እንዳለባቸዉ ለመወሰን ስለተፈጠረዉ ነገር እዉነታ መሰብሰብ አለባቸዉ፡፡ ማንኛዉም የአደጋዉ አካል የነበረዉን ሰዉ ወይ አደጋዉን ያየ ወይ የሰማዉን ሰዉ ሊያናግሩ ይችላሉ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ላይ ጠባሳ ወይ ደም፣ የተቀደደ ልብስ ወይ የተሰበረ የቤት እቃ የመሳሰሉ ‹አካላዊ ማስረጃ› ለማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ ፖሊስ በሰማዉ ወይ ባየዉና በመሰከረዉና እንዲሁም የተጎጂ ቃል መሰረት ወንጀል መፈፀሙንና መታሰር ያለበት ሰዉ እንዳለ ይወስናሉ፡፡
አንድአንዴ ፖሊስ በቦታዉ ሲደርስ ሰዉን ሊያስር ይችላል፤ አንዳኣንዴም ቆይተዉ ሊያስሩ ይችላሉ፤ እንዲሁም አንዳኣንዴ ማንንም ላያስሩ ይችላሉ፡፡ አብዛኛዉ በቤተሰብ ጥቃት ጉዳይ ላይ፣ ፖሊስ ማንኛዉም ወንጀል ፈፀመ ብለዉ ያሰቡትን ሰዉ፣ በእዉነታ መሰረት በቁጥጥር ስር ያዉላሉ፡፡
በአብዛኛዉ የሜርላንድ ማሕበረሰብ የህግ አስከባሪ አባላት የዳኑትን ሰዎች ከአካባብያዊ ጥቃት ኤጀንሲ ጋር እንዲገናኙ በመደገፍ ወይ እራሶ እንዲደዉሉ በማበረታታት የሰለጠኑ ናቸዉ፡፡ የሜርላንድ የቤት ዉስጥ ጥቃት ኤጀንሲ ደህንነቶን እንዲጠበቅና ጥቃት የፈፀመቦት ሰዉ ለተግባሩ/ለተግባሯ እንዲጠየቁ ከአካባብያዊ ሕግ አስከባሪ ኤጀንሲ ጋር በጥብቅ ግንኙነት አብሮ ይሰራል፡፡
ጥቃት የሚደርስበትን ሰዉ እንዴት ማገዝ ይቻላል
ጓደኛን እንዴት ማገዝ ይቻላልየሚያሳስቦትን ነገር ይግለፁ፡፡ ጓደኛዎ በጣም ከባድ፣ እሚያስፈራ ሁኔታ ዉስጥ እንዳለ እዉቅና ይስጡ፡፡ ጓደኛዎን ጥቃቱ የእሱ/የእሷ ጥፋት እንዳልሆነ ያሳዉቆቸዉ፡፡ ጓደኛዎን እንዳመኖቸዉ እና ስለ ደህንነታቸዉ እንደሚጨነቁ ያሳዉቋቸዉ፡፡ ጓደኛዎን ስሜታቸዉን እንዲገልፁና ድጋፍ እንዲያገኙ ያበረታቱ፡፡
ያስታዉሱ ጓደኛዎ ስለዚ ለማዉራት ሊከብደዉ ይችላል፡፡
- የጓደኛዎን ዉሳኔ የመወሰን መብት ያክብሩ፡፡
- ይህንን ቡክሌት ከጓደኛዎ ጋር ይወያዩበት፡፡
- ድጋፍ ሲያስፈልጋቸዉ አብሮ የመሄድ ሃሳብ ያቅርቡ፡፡
- ከጓደኛዎ ጋር ደህንነቱ የተጠበቀ እቅድ ያቅዱ፡፡
የሚያስቡላቸዉ ሰዎች ጥቃት ሲደርስባቸዉ ማየት ከባድ ሊሆን ይችላል፣ እንዲሁም የሚወስኖቸዉ ምርጫዎች ላይረዱት ይችላሉ፡፡ ብሄራዊ የቤት ዉስጥ ጥቃት ሆትላይን በህይወት የሚቆዩ በግንኙነት ዉስጥ ለምን ሊቆዩ እንደሚችሉ የሚገልጽ ትልቅ ብሎግ ፖስት አለው፡፡
ጓደኞቾ እንዴት ሊያግዙ ይችላሉ
- ደህንነቶን ስለመጠበቅ ያሎትን እቅድ የሚያምኑት ሰዉ እንደሚያዉቅ ያረጋግጡ፡፡
- የቤት ዉስጥ ጥቃት ተጠቂ ከሆኑ፣ ለእርሶ የሚያስቡ ሰዎች እንዲያግዞት ይፍቀዱ፡፡
- በሚያምኑት ሰዉ ላይ ይተማመኑ፡፡
- ለእርስዎ ትክክል የመሰሎትን እርምጃ ብቻ ይዉሰዱ፡፡
- ይህንን ቡክሌት ከሚያምኑት ሰዉ ጋር ይነጋገሩበት፡፡
- ከጓደኛዎ ጋር ‹የኣደጋ ጊዜ ሳጥን› ይተዉ፡፡
- ድጋፍ ሲፈልጉ ጓደኛዎ ከእርሶ ጋር እንዲሄዱ ይጠይቁ፡፡
ጥቃት ፈፃሚዎቹን እንዴት ማገዝ እንችላለን
አጋሮቻቸዉ ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎች ድጋፍ ይገኛል፡፡ ጥቃት ፈፃሚዋች የማዳን ፕሮግራም (AIP) በሜርላንድ አጋሮቻቸዉ ላይ ጥቃት ያደርሱ የነበሩት ሰዎች መቀየር እንዲችሉ ያግዛሉ፡፡ በ AIP መሳተፍ በግንኙነት ዉስጥ ለመቆየት ሓይልና ቁጥጥር ከመጠቀም ሌላ የተሻለ አማራጭ እንዳለ ለመማር የመጀመርያ ሂደት ነዉ፡፡ በቡድን አቀማመጥ፣ ተሳታፊዎች ስለ ሓይልና መቆጣጠር፣ በአጋርና ልጆች ላይ የጥቃት ጉዳት፣ አዲስ የግንኙነት ክህሎት ይማራሉ፡፡
AIP ላይ መሳተፍ ጥቃቱ ያቆማል ማለት አይደለም፣ ወደ ጤናማ ግንኙነት ለመቀየር ተነሳሽነት ያላቸዉ ለመምራት እንደ መሳርያ ነዉ፡፡ አንድአንድ ሰዎች የንዴት ማነጅመንት፣ የጥንደዶች ምክር፣ ወይ ሓሺሽና አልኮል ምክር አገልግሎት ጥቃቱን የሚያቆመዉ ይመስላቸዋል፣ ነገር ግን እዉነታዉ ይህ አይደለም፡፡ የጥቃት ፈፃሚዎች የማዳን ፕሮግራም የተገነቡት በተለይ ጥቃትና ቁጥጥር በግንኙነት ዉስጥ ተቀባይነት እንዳለዉ ለተማሩ ነዉ፡፡ የቤተሰብ ጥቃት ምክር ቤት በገዢ ፅሕፈት ቤት የወንጀል ቁጥጥር (GOCCP) በሜርላንድ AIPለመፍቀድ ምክንያት አለዉ፡፡
ሕጋዊ አማራጮች
እርዳታ ቀርቧል/ ምርጫ አሎት
ለዉጥ ማድረግ ወይ በግንኙነቶ ላይ አቋም መዉሰድ ከባድ ሊሆን ይችላል፣ በተለይ አጋሮን እሚፈሩ ከሆነ፡፡ ከቤት መዉጣት፣ መጣላት ወይ ሕጋዊ ተግባር መዉሰድ ለእርሶና ለቤተሰቦ አደገኛ ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ በባለቤቶ፣ አጋሮ ወይ የቤተሰብ አባል እየተጎዱ ከሆነ፣ እርሶንና ልጆቾን ለመጠበቅ እንዲያግዞት ድጋፍ ቀርቧል፡፡
ይህ ገፅ ሲቪል የጥበቃ ትእዛዝ ወይ ሰላም ትእዛዝ ዝርዝር መረጃ በሜሪላንድ (አንድአንድ ጊዜ ‹የእገዳ ትእዛዝ› ወይ ‹ኤክስ ፓርቲ›) ጨምሮ የተለያዩ የደህንነት እቅድ አማራጮችን ያሳያል፡፡ ምንም እንኳን የጥበቃ ወይ ሰላም ትእዛዝ ማመልከት ለእርሶ ጥሩ ዉሳኔ መሆኑን ባያምኑም ቢያምኑም፣ እባኮትን ሌሎች አማራጮችንና የደህንነት እቅድ ስለመፍጠር ለመወያየት የአካባብያዊ የቤት ዉስጥ ጥቃት ፕሮግራምን ይደዉሉ፡፡
አንድአንድ ሰዎች የጥበቃና ሰላም ትእዛዞች የሚያወጡበት ምክንያት ጥቃቱ በፍጥነት እንዲያቆም ስለሚፈልጉ ስለቤት፣ ልጆችና የፋይናንስ ድጋፍ የመሳሰሉ ነገሮች ለማብራራት የፍርድ ቤቱን ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ አብዛኞቹ አገጋሚዎች የሰላምና ጥበቃ ትእዛዝ አጋዥነቱን ቢያምኑም፣ ነገር ግን ትእዛዝ ማዉጣት የሆነ ሰዉ አጠገቦ ከመምጣት ወይ ከመጉዳት አያድኖትም፣ አንድአንድ ሁኔታዎች ላይ ያናድዳቸዋል እንዲሁም አደገኛ ያደርጋቸዋል፡፡ የጥበቃ ትእዛዝ ቢኖሮትም ወደ መጠለያ ወይ ሌላ ደህንነቱ የተጠበወ ቦታ መሄድ ሊኖርቦት ይችላል፡፡ ነገር ግን ትእዛዙ ከተጣሰ ፖሊስ ቶሎ እንዲመልስ ትልቅ ብቃት ይሰጣቸዋል፡፡ ምንም እንኳን የሰላም ወይ የጥበቃ ትእዛዝ ባያገኙም፣ከአጋሮ ጋር ሌሎች ሕጋዊ ጉዳዮች ((ፍቺ፣የማሳደግ ክርክር፣ ወይ ወንጀል) ሊኖሮት ይችላል፡፡
24- አገልግሎት አለ!
ፍርድ ቤቶች ቢዘጉም እንኳን፣ የጥበቃ ወይ ሰላም ትእዛዝ ለያገኙ ይችላሉ! ቅዳሜና እሁድ፣ በባዓላትና ማታ፣ ‹ጊዝያዊ› የጥበቃ ወይ ሰላም ትእዛዝ ከአካባብያዊ ፍርድ ቤት ኮሚሽነር ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ይህ ፍርድ ቤቶቹ እስኪከፈቱ ለተወሰኑ ቀናትና ለአንድ ወይ ከዛ በላይ ሳምንታት የሚቆይ ሌላ የፍርድ ሂደት ፕሮግራም ‹ጊዝያዊ› የጥበቃ ወይ ሰላም ትእዛዝ እስኪፈቀድ ተግባር ላይ ይዉላሉ፡፡ ከዚ በመቀጠል፣ ‹የመጨረሻ› የጥበቃ ወይ ሰላም ትእዛዝ ፍርድ ሂደት ፕሮግራም ይያዛል፣ ከስድስት ወራት እስከ ዓመት፣ ከዛም በላይ ሊቆይ ይችላል፡፡
ጥቃት ምንድን ነዉ?ለሰላም ወይ ጥበቃ ትእዛዝ ብቁ ለመሆን፣ እርስዎ እንደ ተጠቂ ወይ ‹አቤቱታ አቅራቢ›፣ በሜሪላንድ ሕግ እንደተገለፀዉ የጥቃት ተጠቂ መሆን አለቦት፡፡ እሚያካትተዉ፡
- በዉሸት እስራት- የሆነ ቦታ ያለፍቃዶ ማቆየት
- አካላዊ ጉዳት የሚያደርስ ተግባር
- የሰዉነት ጉዳት ፍርሃት ያስገባዎት ተግባር
- በሆነ መጠን ጥቃት
- ያለቀ ወይ የተሞከረ አስገድዶ መድፈር ወይ ፆታዊ ጥቃት
- መድባት/እገዳ
ለሰላም ትእዛዝ፣ በተጨማሪም እነዚ ነገሮች ካጋጠሞት ብቁ ኖት፡
- ጥቃት
- ያለፍቃድ መግባት
- ሆን ብሎ ንብረት ማጥፋት
የሰዓት ገደብ ላይ ማስታወሻ
- በሰላም ትእዛዝ ስር፣ የጥቃቱ ተግባር ባለፉት 30 ቀናት ዉስጥ መፈጠር አለበት፡፡
- በሰላም ትእዛዝ ስር፣ የጥቃቱ ተግባር በማንኛዉም ባለፉት ጊዝያት ሊፈጠር ይችላል፡፡ ነገር ግን፣ በተቻለ ፍጥነት እንዲያመለክቱ ይመከራል፡፡
የትኛዉን ትእዛዝ ባወጣ ይሻለኛል?
በ ‹ጥቃት› (ፍቺ ከታች አለ) እየደረሰቦት ከሆነ የመከላከያ ትእዛዝ ለማዉጣት ማመልከት ብቁኖት፣ ፡
- የአሁን ወይ የድሮ የትዳር አጋር
- አብረዉ ልጅ ያፈሩበት ሰዉ
- ካለፈዉ ዓመት ዉጪ ቢያንስ ለ90 ቀናት አብርዎት የኖረ ጾታዊ አጋር (‹ኮሃቢታንት›)
- ባለፉት ዓመታት ዉስጥ ቢያንስ ለ90 ቀናት አብሮት የኖረ ወላጅ፣ እንጀራ ወላጅ፣ ልጅ፣ ወይ የንጀራ ልጅ
- በዘር፣ ጋብቻ ወይ ማደጎ የተዛመዱት ማንኛዉም ሰዉ
- ፒቲሽን ከማስገባቶ አንድ ዓመት በፊት ከጥቃት ፈፃሚ ጋር ፆታዊ ግንኙነት የነበረዉ ግለሰብ
ግንኙነቶ ከላይ ካሉት ዉስጥ አንዱ ካልሆነ(ለምሳሌ፡ ዴት ያደርጉት የነበረ ወይ ዴት እያደረጉት ነገር ግን ፆታዊ ግንኙነት የሌሎት) በምትኩ የሰላም ትእዛዝ ማመልከት ይችላሉ፡፡
መቼና የት ማመልከት እችላለሁ?
ለጊዝያዊ ጥበቃ ትእዛዝ ብቻ፣ በተጨማሪም ከአካባብያዊ ፍርድ ቤት በተለየ በሰርኪዩት ፍርድ ቤት ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡
ወጪ/ክፍያ ማስታወሻ
የጥበቃ ወይ ሰላም ትእዛዝ ለማመልከት ክፍያ የለዉም፡፡ ለሰላም ትእዛዝ፣ ‹ዴቲንግ ግንኙነት› መሆኑን በፎርሙ ላይ ያመልክቱ ወይ የማመልከቻ ክፍያ ይኖራል፡፡
የቀረቡት ጥበቃዎች ምንድን ናቸዉ?
- ከስራዎ፣ ትምህርት ቤት ወይ መኖርያ ይራቁ
- ጥቃት ማድረሱን ያቁሙ ወይ ጥቃት ሊያደርስቦት ማስፈራራት
- ማግኘት ያቁሙ፣ ለማግኘት መሞከር ወይ ጥቃት የሚያደርስቦት
ለኢንተርምና ጊዝያዊ የጥበቃ ትእዛዞች፣ ዳኛዉ ሊያደርገዉ እሚችለዉ፡
- ጥቃት ፈፃሚዉ ሁለታችሁም ከምትኖሩበት ቤት ዉስጥ እንዲወጣ ማዘዝ
- ጥቃት ፈፃሚዉ የህፃናት እንክብካቤ አቅራቢዎ እንዲርቅ ማዘዝ
- ለእርሶ የልጆች ጊዝያዊ የማሳደግ ፍቃድ መስጠት
- አብረዉ እሚኖሩ ከሆነ፣ ለእርሶ የቤቱን ጊዝያዊ ጥቅምና ባለቤትነት መስጠት
- በጥቃት ፈፃሚዎ ያስፈራራዎት ወይ ጉዳት ያደረሰባቸዉ ልጆቾ፣ ጓደኞቾ፣ ቤተሰብ አባላት ወይ የቤት እንስሳ ጥበቃ መስጠት
- የጦር መሳርያዎች ለሕግ አስከባሪዎች የማስረከብ ትእዛዝ
ለአጠቃላይ የጥበቃ ትእዛዝ፣ ለዳኛዉና የሚመለከታቸዉ ተተኪዎችን ሊጠይቁ የሚችሉት፡
- የባለሙያ ማማከር
- ፋይናንሳዊ ድጋፍ
- የጥየቃ ማስተካከል
- ተሽከርካሪ በጊዝያዊነት መጠቀምና ባለቤት መሆን
- ሌሎች ማንኛዉም እርሶን ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ዳኛዉ የሚለያቸዉ ፋታዎች፣ እነዚህም ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኘት፣ የጤና ዋስትና ማቅረብ፣ ወይ ከተለዩ ቦታዎች መራቅ
ለመጨረሻ የጥበቃ ትእዛዞች፣ ዳኛዉ ማድረግ ያለበት፡
- ትእዛዙ በትግባር ላይ እስከዋለ ድረስ ጥቃት ፈፃሚዉ የጦር መሳርያ እንዲያስረክብና ከመያዝ እንዲቆጠብ ማዘዝ
ለሰላም ትእዛዞች፣ ዳኛዉ ጥቃት የሚፈፅምቦትን ሰዉ ሊያዘዉ ይችላል፡
- ፕሮፌሽናል ምክር እንዲሳተፉ
- የማመልከቻ ክፍያና ወጪ እንዲከፍሉ
ገዝያዊ ትእዛዝ መቼ ወደ ተግባር ይወርዳል?
እቤት ከመመለሶ በፊት ወይ ጥቃት ፈፃሚዎ ሊኖርበት በሚችልበት ቦታ ከመሄዶ በፊት፣ መጀመርያ ትእዛዙ እንደደረሰዉ ያረጋግጡ፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ በአካባቢዉ በሚገኘዉ ትእዛዝ ከሚያቀርበዉ የሕግ አስከባሪ ኤጀንሲ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ትእዛዙ እንደተሰጠ የሚያሳዉቅ አገልግሎት በስልክ ወይ በአሜል ለማግኘት ለቫይን ጥበቃ ትእዛዝ (VPO) ሊመዘገቡ ይችላሉ (ማስታወሻ፡VPO አገልግሎት መረጃ በሰላም ትእዛዝ ላይ አያካትትም)፡፡
ጊዝያዊ ትእዛዝ ተቀባይነት እሚኖረዉ እስከ መጨረሻዉ የጥበቃ ትእዛዝ ፍርድ ሂደት ነዉ፡፡ ትእዛዙ እንዲቀጥል እምትፈልጉ ከሆነ፣ የመጨረሻዉን ትእዛዝ ፍርድ ሂደት መካፈሎ አስፈላጊ ነዉ፡፡
የመጨረሻ ትእዛዝ ምንድን ነዉ?
ምስክሮች፣ ፎቶግራፎች፣ የሕክምና የፖሊስ ሪፖርቶች፣ በአደጋዉ ጊዜ የተጠቀሙባቸዉ እቃዎችን ወዘተ.. የመሳሰሉ ማስረጃዎችን ማምጣቶን ያረጋግጡ፡፡ የመጨረሻዉ የሰላም ወይ ጥበቃ ትእዛዝ በዳኛዉ እሚሰጦት፡
- ጥቃት ፈፃሚዎ በትእዛዙ ከተስማማ
ወይ - ዳኛዉ ጥቃቱ የተፈፀመበት ‹አሳማኝ ማስረጃ› ካገኘ ነዉ (ይህ ማለት ጥቃቱ ተፈፅሟል ማለት ይቻላል)፡፡
የመጨረሻዉ ትእዛዝ ምንያህል ጊዜ ይቆያል?
የመጨረሻ የሰላምና ጥበቃ ትእዛዝ ወድያዉኑ ተግባር ላይ ይዉላል፡፡ የጥበቃ ትእዛዝ እስከ 12 ወራት ወይ አንድአንዴም በተወሰኑ ሁኔታዎች ከዛ በላይ ሊቆይ ይችላል፡፡ የሰላም ትእዛዝ እስከ ስድስት ወራት ሊቆይ ይችላል፡፡ የሰላም ወይ ጥበቃ ትእዛዝ ቀኑ ከማለፉ በፊት፣ እንዲራዘምሎት መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የጥበቃ ትእዛዝ እስከ ስድስት ወራት ሊራዘም ይችላል፡፡ በሆነ ሁኔታዎች ላይ፣ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ የሰላም ትእዛዝ በተጨማሪ ለስድስት ወራት ሊቆይ ይችላል፡፡ አንዴ ትእዛዙ ተግባር ላይ ከዋለ፣ መጀመርያ ወደ ታዘዘዉ የፋታ ዓይነት እንዲቀየርሎት፣ የትእዛዝ ‹ማሻሻያ› መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ትእዛዝ ከአሁን ወድያ ካልፈለጉ፣ ‹እንዲ ሰረዝ› መጠየቅ ይችላሉ፣ ማለትም ‹ተትቷል› ማለት ነዉ (ማለትም ከአሁን በሆላ ተግባር ላይ አይዉልም)፡፡
ጥቃት ፈፃሚዉ ትእዛዙን ከጣሰ ምን ይፈጠራል?
የሕግ አስከባሪዎች ጥቃት ፈፃሚዉ ‹አለማግኘት› ወይ ‹መራቅ› የሚለዉን የኢንተርም፣ ጊዝያዊ ወይ መጨረሻ የጥበቃ ወይ ሰላም ትእዛዝ ክፍል በመጣስ በቁጥጥር ስር ሊያዉሎቸዉ ይጠበቃል፡፡ ጥሰት አስከ 90 ቀናት በእስር ቤት ዉስጥ መቆየት እና/ወይ $1,000 የቅጣት ክፍያ ይጠብቃል፡፡
ለጥበቃ ትእዛዝ፣ ሁሉም ተከታታይ ጥሰቶች በሆላ እስከ አንድ ዓመት እስር ወይ $2500 የቅጣት ክፍያ ያስከትላል፡፡
ጥቃት ፈፃሚዉ ሌሎች ያሉትን የጥበቃ ትእዛዝ ከጣሱ (የልጆች ማሳደግ ፍቃድ፣ ጥየቃ፣ ፋይናንሳዊ ድጋፍ፣ ምክር፣ የጦር መሳርያ)፣ ‹ፍርድ ሂደት በማዛባት› ሊያዝ ይችላል፡፡
ለሰላም ስርዓቶች፣ ጥቃት ፈፃሚዎ ሌሎች የተቀመጡት ከጣሰ (ምክር መሳተፍ፣ ቅጣት መክፈል ወዘተ..)‹ፍርድ ሂደት በማዛባት› ሊያዝ ይችላል፡፡
በፍርድ ቤት የፍርድ ትእዛዝ ላይ ደህንነቶን የመጠበቅ እቅድ
ከፍርድ ቤት በፊት፡
በፍርድ ቤት በጊዜ ይድረሱ እንዲሁም ከቻሉ ደህንነቱ የተጠበቀና ታማኝ ሰዉ ይዘዉ ይምጡ፡፡ ይህ ጓደኛ፣ ደጋፊ ወይ ከአካባብያዊ የቤት ዉስጥ ጥቃት ፕሮግራም ጠበቃ (ገፅ 1 ይመልከቱ)፣ ወይ የራሶን የግል ጠበቃ ሊያካትት ይችላል፡፡
ወደ ፍረድ ቤቱ ከመጠራታቸዉ በፊት የተደበቀ ሊቆዩበት የመችሉበት ቦታ ካለ ይጠይቁ፡፡
በፍረድ ቤት፤
በጥቃት ፈጻሚዉ፣ ጓደኛና ቤተሰብ ወዘተ.. አጠገብ ሊቀመጡ ወይ ሊቆሙ እንዲሁም ለማየት ስሜታዊ ዝግጅት ማድረግ አለባቸዉ፡፡ ይህ አስፈሪ ወይ የሚያስደነግጥ ሊሆን ይችላል ስለሆነም ማበረታቻና ጥንካሬ ሊሰጦት የሚችል የሆነ ሰዉ ወይ እንደ ማስታወሻ፣ መፅሓፍ፣ ጌጥ ወይ ፎቶ የመሳሰሉ ነገሮች መያዝ አስፈላጊ ነዉ፡፡
ጥቃት ፈፃሚዉ ፍርድ ቤት ዉስጥ በጽሑፍ መልእክት፣ ኢሜል፣ ምልክት ወይ ሊያናግሮት ከሞከረ ደጋፊዎን፣ ጠበቃዎን ወይ ዳኛዉን መንገር ይችላሉ፡፡
ከፍርድ ቤት በሆላ፡
ፍርድ ቤቱ የሚወጡበትን ቦታ ካልገለፀ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የሚያምኑት ሰዉ ወደ መኪናዎ፣ አዉቶቢስ እንዲያደርሶ፣ ወይ ወደ ቤቶ እንዲመልሶ ያድርጉ፡፡ ከጥቃት ፈፃሚዎ 10 ደቂቃ በፊት እንዲለቆት ፍርድ ቤቱን መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ደህንነት ካልተሰማዎት ዳኛዉን ወይ ፍርድ አስፈፃሚዉን አጃቢ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አንዴ የሰላም ወይ ጥበቃ ትእዛዝ ከተቀበሉ በሆላ ግልባጩን ሁሉም ግዜ ይያዙት፡፡ የትእዛዙን ግልባጭና የጥቃት ፈፃሚዉን ፎቶ ለሚያምኑት ሰዉ፣ ጎሮቤት፣ አሰሪ፣ ትምህርት ቤት፣ የህፃናት ማቆያ፣ ወዘተ.. ይስጡ፡፡
ለሚያምኖቸዉ ሰዎች ትእዛዝ እንዳወጡና አሁንም አደጋ ላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይንገሩ፡፡ ጥቃት ፈጻሚዉ ከቀረባቸዉ ወይ ካገኛቸዉ ማድረግ ያለባቸዉን ትእዛዝ ይስጦቸዉ፡፡
በደህና መሰንበት
ጥቃት ያለበት ግንኙነት ላይ ከሆኑ ምን ማድረግ እንዳለቦት መወሰን ቢከብዶት የተለመደ ነዉ፡፡ ብቻዎትን አይደሉም፡፡ ድጋፍ አለ፡፡ ግምት ዉስጥ ሊስገቧች እሚገቡ አማራጮችና ጉዳዮች፡
አማራጮችናግንኙነቱ ዉስጥ መቆየት
ከቆዩ፣ ድጋፍና ደህንነት ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ስም ጠርተዉ ከነበር፣ እራሶን በስሜት እንዴት መንከባከብ ይቻላል? አደገኛ ከሆነ ወይ እረፍት ከፈለጉ ሊቆዩበት እሚችሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ አለ?
ለመተዉ ማቀድ
ምናልባት ለመተዉ ቢፈልጉ፣ እቅድ ይፈልጋል፡፡ ብር እንዴት ማግኘት ይችላሉ? በቤቶ ደህንነቶ ይጠበቃል? መቼ መዉጣት ይችላሉ? ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳሉ? ጠበቃ ይፈልጋሉ? አጋሮ እንዴት ምላሽ ይሰጣል? ደህንነቶ እንደተጠበቀ እንዳይወጡ ምን ያግዶታል? በስዓቱና በድጋፍ፣ ለመዉጣት እቅድ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ግንኙነት መተዉ
ለመዉጣት ከወሰኑ፣ አደጋ ላይ ከሆኑ የሚያስፈራ ትልቅ የሂወት ለዉጥ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዳይገኙ መቀየር ወይ ስራ መቀየር አለቦት? ለተወሰኑ ጓደኞች ማዉራት ማቆም? ከማሕበራዊ ሚድያ እረፍት መዉሰድ? የጥበቃ ትእዛዝ ማዉጣት ወይ ፖሊስ ጋር መደወል? ለማሰብ ከባድ ቢሆንም፣ አዲስ ሂወት ይቻላል፡፡
የድጋፍና ደህንነት እቅድ
ምንም ቢወሰወኑ፣ የድጋፍ ሲስተም ሊገነቡና ደህና ለመሆን መንገድ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
የአጋሮን የጥቃት ፀባይ መቆጣጠር አይችሉም ነገር ግን እርሶንና ልጆን ከጥቃት ለመከላከል እርምጃ መዉሰድ ይችላሉ፡፡ ሁኔታዎን ለማወቅ ትክክለኛዉ ሰዉ እርሶ ኖት፡፡ በቤቱ ወይ ግንኙነቱ ላይ መቆየት አደገኛ እሚሆንበትን ወቅት ያዉቃሉ፡፡ በግንኙነቱ ላይ መቆየት ወይ ለመተዉ ከወሰኑ፣ የደህንነት እቅድ መፍጠርን ያስቡ፡፡
የደህንነት እቅድ እርሶንና ልጆቾን በቤት፣ ትምህርት ቤት፣ ስራና በማሕበረሰብ በተሻለ ለመጠበቅ ነገሮችን ለመለየት እንዲያግዞት ግላዊና ተግባራዊ እቅድ ነዉ፡፡ በተጨማሪም የመጎዳት አደጋዉን ለመቀነስ ያግዛል፡፡ የሚፈጠረዉ ለዉጥ ትልቅ ሊሆን ይችላል፣ ሚስጢራዊ መጠለየ መሄድ ወይ ትምህርት ቤት መቀየር ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም እንደ ኢሜል ሚስጢር ቁጥር መቀየር ወይ የመስርያ ቤት መንገድ መቀየር ትንሽ ለዉጥ ሊሆን ይችላል፡፡ አስቀድሞ እቅድ ማዉጣት በጥቃቱ ወቅት ወይ በሆላ ደህንነቶን እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡ የደህንነት እቅዶ ደህንነቶ እንደተጠበቀ እርሶና ልጆቾ ከጥቃት እንዲያመልጡና ድጋፍ ከፈለጉ እንዲያገኙ ሊያግዞት ይችላል፡፡
የቴክኖሎጂ ደህንነት
አጋሮ በቴክኖሎጂ አድርጎ እየተከታተሎት ወይ እያስቸገሮት ከሆነ ምን ማድረግ ይችላሉ?
ጥቃቱን ይመዝግቡ
የመታገት መጥፎ አጋጣሚ ሎግ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ከአጋቹ ጋር የሚደረግ የጉትጎታ የድምጽ መልእክት፣ ጽሑፍ፣ ኢሜል መልእክትና የኦንላይን መልእክትና ሁሉኑም ግንኙነት ሪከርድ ያድርጉ፡፡ የኢሜልና ኦንላይን መልእክቶችን ከስክሪን ሾት በማንሳት ፕሪንት ስክሪን ቁልፍ በመጠቀም ዎርድ ዶክሜንት ላይ ይገልብጦቸዉ፡፡ ሁሉኑም መረጃዎች መስቀመጦን ያረጋግጡ፣ በተለይ የፖሊስ ሪፖርትና ሕጋዊ መረጃዎች፡፡ የእነዚህን ማተርያሎች ግልባጮች ለሚያምኑት ሰዉ ይስጡ፡፡
ስልክ ላይ
- አዲስ ስልክ ይግዙና ቁጥሩን በሚስጥር ይያዙት፡፡
- የሚያደባዉን ሰዉ ጥሪና ፅሑፍ ለመያዝ የድሮ ስልኮን ያስቀምጡ፡፡
- የሚስጢር ቅንብሮንና አካባቢ ተከታታይ መተግበርያዎን በስልኮ ላይ ይፈልጉ፡፡
- የስልኮን አካባቢ አገልግሎት በ ቅንብር —> ሚስጢር —> የአካባቢ አገልግሎት ያጥፉ፡፡
- የማስፈራርያ ጥሪዎችን ለስልክ ድርጅቶ ወይ ለፖሊስ ያመልክቱ፡፡
ኮምፒዩተሩ ላይ
- አብዛኛዉ የማሕበራዊ ድህረ ገፅ መድረኮች የመከታተል ስራ አላቸዉ፡፡ እዛ ካለ አይተዉ ያረጋግጡ፡፡ ያስተዉሉ እርሶ ሳያዉቁ ሌላ ሰዉ መከታተያዉን መልሶ አብርቶት ሊሆን ይችላል፡፡
- ግላዊ ኮምፒዩተሮ ሃክ ተደርጎ ወይ ተጠልፎ ሊሆን ይችላል፡፡ ደህንነቱ የተጠበቀ ኮምፒዩተር በጓደኛዎ፣ ስራ ወይ መፅሓፍት ቤት ያግኙ፡፡
- ለተጨማሪ ጥበቃ አንቲ ቫይረስና አንቲ ስፓይዌር ይግዙ፡፡ አንዴ ገብያ ላይ ከዋሉ የወጪ መቀነስ አለ፡፡
- ከባድ፣ የተወሳሰበ ሚስጢር ቁጥርና ለያንድአንዱ አካዉንት የተለያየ ሚስጢር ቁጥር ይጠቀሙ፡፡ ትክክለኛ ስሞ፣ ልደት ወይ አካባቢ የመሳሰሉ ግላዊ መረጃዎች አይጠቀሙ፡፡ ተጨማሪ የሚስጥር ቁጥር ጥበቃ ለመጨመር እንደ ላስት ፓስና ኪፐር የመሳሰሉ ፕሮግራሞችን ማዉረድ ይችላሉ፡፡
- ለመረጃዎ የድህረ ገፅ ፍለጋ ያድርጉ፡፡ ስለ እራሶ ሰዉ እንዲያቀዉ የማይፈልጉት መረጃ ኦንላይን ላይ ካገኙ፣ ድህረ ገፁ መረጃዉን እንዲያጠፉት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- በኦንላይን ላይ የሚለጥፉትንና የሚያጋሩትን ነገር ያስተዉሉ፡፡ ምንም እንኳን ቢያጠፉትም፣ በኦንላይን ላይ ለዘላለም ይቆያል፡፡
በቤት ዉስጥ በሚሆኑበት ወቅት
- አድራሻዎን በሚስጢር ለመያዝ እንዲያግዞት፣ ሚስጥራዊ የመልእክት መላክያ አገልግሎት፣ የሜሪላንድ ደህንነት በቤት አድራሻዎች ሚስጢራዊ ፕሮግራም በነፃ ያመልክቱ፡፡ የበለጠ ለመማርና ለማመልከት በብሮሸሩ ላይ ያለዉን አካባብያዊ የቤት ዉስጥ ጥቃት ኤጀንሲ ያግኙ፡፡
- የደህንነት ሲስተም፣ የቤት ካሜራ ወይ የእንቅስቃሴ መለያ መብራት ይግጠሙ፡፡
- የቤቶን ወይ የሜኪናዎን ቁልፍ ይቀይሩ እንዲሁም ሁሉ ግዜ በሮንና መስኮቶን ይቆልፉ፡፡
ሪሶርስ
አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ሪሶርሶች ከታች አሉ፡፡ እነዚህን ዶክሜንቶችን ሊያዩና ፕሪንት ሊያደርጉ ይችላሉ፣ ነገር ግን እባኮትን ደህንነቱ የተጠበቀ ኮምፒዩተር ላይ ዳዉንሎድ ያድርጉ፡፡
በተደጋጋሚ ጥያቄ ጠይቅያለሁ
ጥቃት ያለበት ግንኙነት ላይ ነኝ፡፡ ለድጋፍ የት መሄድ አለብኝ?አካባብያዊ የቤት ዉስጥ ጥቃት ኤጀንሲዎን 24/7 ሊደዉሉ ይችላሉ፡፡ እርሶን ወይ ያሉበትን ሁኔታ ሳይገመግም በጥንቃቄ እሚሰማዎትና የሚያስብሎትን ሰዉ ጋር ያወራሉ፡፡ ደጋፊዎቹ ስላሎት አማራጮችና እሚወሰዱ ሂደቶችና ለርሶ ከሚጠቅም አገልግሎቶች ለመለየት ይረዳዎታል፡፡ ደጋፊዎቹ ስለ ሁኔታዎ ለማወቅ ጥያቄ ሊጠይቁ ይችላሉ ነገር ግን የእርሶን መሪነት ይከተላል፡፡ ለእርስዎ ጥሩ የሆነዉን እንደሚያቁ ባያስቡም፣ ለእርሶና ልጆቾ ጥሩ ሂደትና የተግባር ዉሳኔ እንዲወስኑ፣ ሁሉኑም ሊሆኑ የሚችሉ የወደፊት ሁኔታዎችና ዉጤቶች ግምት ዉስጥ እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ፡፡
እያንዳንዱ ሰፊ የቤት ዉስጥ ጥቃት ኤጀንሲ ከሁሉም ዘር፣ ብሄር፣ ዕድሜ፣ ፆታ፣ ማንነት፣ የፆታ ፍላጎት፣ ችሎታ፣ ባህል፣ መነሻ፣ ባህልና ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ መነሻ ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ አገልግሎቱ ነፃና ሚስጢር ናቸዉ፡፡ ዶክሜንት ከሌሎት ወደ ኢሚግሬሽን ፣ICE ፣ ወይ የሕግ አስከባሪ ሪፖርት አይደረግቦትም፡፡
ምን ዓይነት አማራጮች አሉኝ?
ጥበቃ ትእዛዝ ከማግኘት ጀምሮ፣ በመጠለያ እስከ መቆየት ወይ በድጋፍ ቡድን ወይ በማይታወቅ ጥሪ ወደ አካባብያዊ ፕሮግራም በማድረግ ጨምሮ ብዙ አማራጭ አልዎት፡፡ ተስፋ ኣለ፡፡ ብቻዎትን አይደሉም፡፡ እዚ ስላሎት ምርጫዎች በይበልጥ ይማሩ፡፡
ጥቃት ፈፃሚዉ የመቀየር እድል አለዉ?
ወንዶች የቤት ዉስጥ ጥቃት ተጠቂ ናቸዉ?
ተጠቂዎቹ ለምን ግንኙነቱን አይተዉትም?
- ፍቅር፡ ተጠቂዎቹ ሁሉም ግዜ የተጎዱ አይደሉም፡፡ አብዛኞቹ ጥቃት ፈፃሚዎች እሚወደድና እሚፈቀር ጎን አላቸዉ፡፡ እሚበዙት ተጠቂዎች ጥቃት ፈፃሚዉን ባህሪ መቀየር እሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡
- ፍርሃት፡ ተጠቂዎቹ ለመዉጣት ከወሰኑ እሚበዙት ጥቃት ፈፃሚዎች ራሳቸዉን ለመጉዳት ወይ ለመግደል ያስፈራራሉ፡፡ አብዛኛዉን ግዜ ጥቃት ፈፃሚዎች አጋራቸዉ ለመዉጣት ከወሰኑ ጥቃቱ እንደሚባባስ ያስፈራራሉ፡፡ በመጨረሻም፣ አደገኛ እሚሆነዉ ተጠቂዋ ለመዉጣት በምትሞክርበት ወቅት ነዉ፡፡
- ጥርጣሬ፡ ተጠቂዉ ሁሉም ጊዜ ጥቃት ያለበት ግንኙነት ዉስጥ እንዳሉ ማመን ቀላል አይደለም፡፡ በተለይ የተጠቂዉ አጋር በትምህርት ቤት ወይ በማሕበረሰቡ ዉስጥ ተወዳጅ ከሆነ፣ ተጠቂዉ ማሕበራዊ ሁኔታዉን እንዳያጡ ሊጨነቁ ይችላሉ፡፡
- እፍረት፡ ተጠቂዉን ከዚ በፊት ሊያግዙት ከሞከሩት ሰዎች ‹ብዮ ነበረ› እሚለዉን ነገር ፈርተዉ ሊሆን ይችላል፡፡
- ለለዉጥ ተስፋ፡ አብዛኛዉን ግዜ ተጠቂዎች ጥቃት ፈፃሚዉ በግንኙነቱ መጀመርያ የነበራቸዉ- በፍቅር የወደቁለት ሰዉ እንደሚመለስ ያምናሉ፡፡
- መገለል፡ እንደ ጥቃት ስልት፣ ጥቃት ፈፃሚዉ ለተጠቂዉ ሃብትና ደጋፊ ሰዎች በማግኘት ላይ ከባድ ሊያደርገዉ ይችላል፡፡
- ማሕበረሳባዊ አለማመን፡ አብዛኛዉን ግዜ ጥቃት ፈፃሚዎች በህብረተሰቡ ፊት አማላይና ግርማ ሞገስ አላቸዉ፡ ይህንን ብቻ ለሚያዉቁ ሰዎች ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑን ለማመን ከባድ ነዉ፡፡
- ማሕበረሰባዊ ግምት፡ ተጠቂዉ ግንኙነቱን ማቆም እንደ ዉድቀት ሊያየዉ ይችላል እንዲሁም በሕብረተሰቡ መጥፎ ስም ሊፈራ ይችላል፡፡ ተጠቂዎቹ ስለ ተጠቂዎች የቤት ዉስጥ ጥቃት ስቲርዮታይፕ ላይመጣጠኑ ይችላሉ፡፡
- የሃብት እጥረት፡ተጎጂዎቹ ደጋፊ ሰዎች ለማግኘት ከባድ ወይ እማይቻል ሊሆን ይችላል፣ እንዲሁም ብር ወይ እቤቱን ለማግኘት መንገድ የሌላት ሊሆን ይችላል፡፡
እየቀጠሩ ነዉ?
ጀማሪዎችን ይቀጥራሉ?
አንድአንዴ! እዚህ ያጣሩ፡፡
በጎፈቃደኞችን ይቀበላሉ?
ከሚያገግሙ ሰዎች ጋር በጎ ፈቃድ ለመስጠት ፍላጎት ካሎት፣ ጥቃት ለማቆምና ተጠቂዎች ሂወታቸዉን ዳግም እንዲገነቡ ዝግጁ የሆኑ ፕሮግራሞች በመላዉ ሜሪላንድ ዉስጥ አሉ፡፡አጠገቦ የሚገኙትን በጎ ፍቃድኞች እሚፈልጉ ፕሮግራሞች ለማግኘት፣ እዚህ ይጫኑ፡፡
ቡድኔን ማሰልጠን ይችላሉ?
ለስልጠናዎ CEU ያቀርባሉ?
MNADV ለፍቃድ ያለዉ ማሕበራዊ ሰራተኞች በሜሪላንድ የማሕበራዊ ሰራተኛ ኤግዛማይነር ቦርድ ተከታታይ ትምህርት ክሬዲት(CEU) እንዲያቀርቡ ፍቃድ ተሰጦታል፡፡ አብዛኞቹ MNADV ስልጠናዎች ቀጣይ ትምህር ክሬዲት ቀርቧል (ይህ መረጃ ለስልጠናዉ ፍላየሩ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ምዝገባ ላይ ነዉ )፡፡
ማሕበራዊ ስራ CEU ለግላዊ አባላትና በአባል ድርጅቶች አባል ሰራተኞች በነፃ ቀርቧል፡፡ የMNADV አባል ለመሆን ለበለጠ መረጃ፣ በድህረ ገፅ እዚ ይሂዱ፡፡
አባላት ላልሆኑ ሰዎችና ማሕበራዊ ስራ CEU መስራት እሚፈልጉ፣ በትንሽ ገንዘብ ሊገዙ ይችላሉ፡፡ እዚ የበለጠ መረጃ፡፡
ስለ ቤት ዉስጥ ጥቃት ምን ማድረግ እችላለሁ?
-
- ይማሩ
ስለ ቤት ዉስጥ ጥቃትና በሱ ዙርያ ያሉትን ጉዳዮች መማር ሁሉም ቦታ እንዳለ እንዲገነዘቡ ያግዛል፡፡ - ይቃዎሙ
ሁሉም ሰዉ የቤት ዉስጥ ጥቃት ተቃዉሞ መቆም ይችላል፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ድምፅ ‹ከአሁን በሆላ ይብቃ› ብሎ ካልቆመ ችግሩ ይቀጥላል፡፡ በተጨማሪም የህዝብ ፅሕፈት ቤቶን በመደወል የሂወት ቁጠባ ድጋፍ ለቤት ዉስጥ ጥቃት አገልግሎትና ጥፋተኞችን የሚገባቸዉን እንዲያገኙ ማገዝ ይችላሉ፡፡
- በጎ ፈቃደኛ
በጎ ፍቃደኝነት ካሰቡ፣ ጊዜዎን ለቤት ዉስጥ ጥቃት አገልግሎት አቅራቢ ያዉሉት፡፡ የቤት ዉስጥ ጥቃት በማስቆም ላይ እንዲያግዙ ብቻ ሳይሆን፣ በጉዳዩ ላይ የተሻለ አስተሳሰብ እንዲኖሮት ያግዛል፡፡ - እርዳታ
MNADV በቀጥታ ወይ በማንኛዉም በሜርላንድ አስደናቂ አካባብያዊ ጥቃት ፕሮግራም ላይ እርዳታ መስጠት ይችላሉ፡፡
- ይማሩ